ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን ታላላቅ ገዳማት ለመጡ አበምኔቶችና እመምኔቶች አቀባበል ተደረገ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን
የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ
ለማሳካት የገዳማት ድርሻ በሚል በተዘጋጀው ዐውደ ጥናትና ለአምስት ቀናት በሚቆየው ሥልጠና፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ አሻራቸውን ትተው ያለፉትን የታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የገድል መጽሐፍ ምረቃ ላይ ለመገኘት ከሃምሳ በላይ ለሚደርሱ ገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች በተደረገው ጥሪ መሠረት
ከማክሰኞ ጀምሮ ርቀቱ ሳይገድባቸው አዲስ አበባ በመግባት ላይ ሰንብተዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም ዝግጅቱን አጠናቆ
በጉጉት ከመጠባበቅ አልፎ በአክብሮት እየተቀበላቸው ይገኛል፡፡
No comments:
Post a Comment